Skip to content
Text size 100%
Translation comparison

Compare Az-Zalzalah in Amharic

Compare up to three translations verse by verse.

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِذَا زُلْزِلَتِ ٱلْأَرْضُ زِلْزَالَهَا ﴿1﴾

Amharic Translation - Muhammad Sadiq

ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤

وَأَخْرَجَتِ ٱلْأَرْضُ أَثْقَالَهَا ﴿2﴾

Amharic Translation - Muhammad Sadiq

ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤

وَقَالَ ٱلْإِنسَٰنُ مَا لَهَا ﴿3﴾

Amharic Translation - Muhammad Sadiq

ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤

يَوْمَئِذٍۢ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا ﴿4﴾

Amharic Translation - Muhammad Sadiq

በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡

بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا ﴿5﴾

Amharic Translation - Muhammad Sadiq

ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡

يَوْمَئِذٍۢ يَصْدُرُ ٱلنَّاسُ أَشْتَاتًۭا لِّيُرَوْا۟ أَعْمَٰلَهُمْ ﴿6﴾

Amharic Translation - Muhammad Sadiq

በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡

فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًۭا يَرَهُۥ ﴿7﴾

Amharic Translation - Muhammad Sadiq

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍۢ شَرًّۭا يَرَهُۥ ﴿8﴾

Amharic Translation - Muhammad Sadiq

የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

Quran recitationReady
Open audio