تجاوز إلى المحتوى

የነቢዩ ﷺ የህይወት ታሪክ ክፍል

32 lessons · Select a question to read the answer

Your progress in this topicTrack completed lessons on this device
Choose how to study:
1ጥያቄ 1፡ የነቢያችን ሙሐመድ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንን የዘር ሀረግ ጥቀስ?

መልስ - እሳቸው የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙሐመድ ብን ዐብደላህ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ ቢን ሀሺም ናቸው፤ ሀሺም ከቁረይሽ ዘር ነው፤ ቁረይሾችም ከዐረብ ዝርያዎች ናቸው፤ ዐረቦች ደግሞ የኢስማዒል ዘር ሲሆኑ ኢስማዒል ደግሞ የኢብራሂም ዘር ናቸው። በሳቸውም በነብያችንም በላጭ የሆነው የአላህ ሰላዋትና ሰላም ይስፈንባቸውና።

Open lesson
2ጥያቄ 2፡ የነቢያችን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እናት ስም ማን ይባላል?

መልስ- አሚና ቢንት ወህብ ትባላለች።

Open lesson
3ጥ3: አባታቸው የሞተው መቼ ነው?

መልስ- አባታቸው የሞተው እርሳቸው የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ገና ሳይወለዱ በእርግዝና ሳሉ ነበር።

Open lesson
4ጥ 4፡ ነብዩ ﷺ የተወለዱት መቼ ነው?

መልስ- የዝሆን አመት ተብሎ በተሰየመው አመት በወርሀ ረቢዐል አወል እለተ ሰኞ ነው።

Open lesson
5ጥ5: የት ሀገር ተወለዱ?

መልስ - በመካ።

Open lesson
6ጥ 6፡ ከእናታቸው ውጭ ተንከባካካቢያቸው እና አጥቢያቸው ማን ነበረች?

መልስ - የአባታቸው ባሪያ ኡሙ አይመን፤

- የአጎታቸው አቡ ለሀብ ባርያ ሡወይባህ፤

- ሐሊመቱ-ስ-ሰዕዲያህ፤

Open lesson
7ጥ7: እናታቸው የሞተችው መቼ ነው?

መልስ - በስድስት ዓመታቸው እናታቸው ስትሞት አያታቸው ዐብዱል ሙጦሊብ ይንከባከቧቸው ጀመር።

Open lesson
8ጥያቄ 8፡ አያታቸው ዐብዱል ሙጦሊብ ከሞቱ በኋላ የተንከባከባቸው ማን ነው?

መልስ- ስምንት አመት ሲሆናቸው አያታቸው ዐብዱል ሙጦሊብ ሞቱና ተንከባካቢያቸው አጎታቸው አቡ ጧሊብ ሆኑ።

Open lesson
9ጥ 9፡ ከአጎታቸው ጋር ወደ ሶርያ የተጓዙት መቼ ነው?

መልስ - ከአጎታቸው ጋር ወደ ሶርያ የሄዱት በአሥራ ሁለት ዓመታቸው ነው።

Open lesson
10ጥ10፡ ሁለተኛው ጉዟቸው መቼ ነበር?

መልስ - ሁለተኛው ጉዟቸው በኸዲጃ ረዲየሏሁ ዓንሀ ገንዘብ ለመገበያየት ያደረጉት ጉዞ ነበር። እሳቸው የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከጉዞ ተመልሰውም እድሜያቸው ሃያ አምስት አመት ሆኖ አገቧት።

Open lesson
11ጥ 11፡ ቁረይሾች ካዕባን መልሰው የገነቡት መቼ ነበር?

መልስ - ቁረይሾች ካዕባን እንደገና የገነቡት የሳቸው ዕድሜ ሠላሳ አምስት ሲሆን ነበር።

ሐጀረል አስወድን ማን እንደሚያስቀምጠው በመካከላቸው የሀሳብ ልዪነት በተነሳ ጊዜ እርሳቸውን ፈራጅ አድርገዋቸው ነበር። እርሳቸውም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንዳች ልብስ አምጥተው ከየጎሳው አንድ አንድ ሰው ተውክሎ የልብሱን ጠርዝ እንዲይዝ አዘዙ። ጎሳዎቹም አራት ነበሩ። የእያንዳንዱ ነገድ ተወካይ ጠርዝ ጠርዙን ይዞ ከፍ እንዳደረገላቸው እሳቸውም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በእጃቸው ተቀብለው ቦታው ላይ አደረጉት።

Open lesson
12ጥ 12፡ አላህ መልዕክተኛው አድርጎ ሲልካቸው እድሜያቸው ስንት ዓመት ነበር? ወደ ማንስ ነው የተላኩት?

መልስ - የአርባ ዓመት ጎልማሳ ነበሩ፤ የተላኩትም ለሰዎች ሁሉ አብሳሪና አስጠንቃቂ ተደርገው ነው።

Open lesson
13ጥ13፡ የመጀመሪያ ወሕይ የወረደላቸው በምን መልኩ ነበር?

መልስ - መጀመርያ ወሕይ (መለኮታዊ ራዕይ) ሲወርድላቸው የነበረው በእውነተኛ ህልም መልኩ ነበር። ምንም ዓይነት ህልም ቢያዩ ልክ እንደ ንጋት ጎህ ፍንትው ብሎ እውን ይሆን ነበር።

Open lesson
14ጥ 14፡ ወሕይ ሳይገለጥላቸው በፊት በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ነበሩ? ወሕይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጠላቸውስ መቼ ነበር?

መልስ- በሒራእ ዋሻ ውስጥ አላህን ያመልኩ እና ለዛም ብለው ስንቅም ይቋጥሩ ነበር።

በዋሻው ውስጥ አላህን እያመለኩ በነበረበት ጊዜም ነበር ወሕይ የወረደላቸው።

Open lesson
15ጥ 15፡ ከቁርኣን ለመጀመሪያ ጊዜ የወረደላቸው ምን የሚለው ነበር?

መልስ- ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም። 1 ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)። 2 አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን፤ 3 ያ በብዕር ያስተማረ። 4 ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን። 5} [አልዓለቅ፡ 1 - 5]

Open lesson
16ጥ 16፡ በመልዕክተኝነታቸው በመጀመሪያ ያመነላቸው ማን ነበር?

መልስ - ከወንዶቹ አቡበከር አስ'ሲዲቅ፤ ከሴቶች ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ፤ ከተዳጊዎች ዐልይ ቢን አቢ ጧሊብ፤ ነፃ ከወጡ ባርያዎች መካከል ዘይድ ቢን ሐሪሣህ እና ባሪያ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቢላል አል'ሐበሺይ ናቸው። አላህ ሁሉንም መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና።

Open lesson
17ጥ 17፡ ወደ እስልምና ዳዕዋ ሲያደርጉ የነበሩት እንዴት ነበር?

መልስ - ዳዕዋ ሲያደርጉ የነበሩት ለሦስት ዓመታት ያህል በምስጢር የነበረ ሲሆን ከዚያም ዳዕዋውን በይፋ እንዲያደርጉ አላህ አዘዛቸው።

Open lesson
18ጥያቄ 18፡ ዳዕዋውን በይፋ ከጀመሩ በኋላ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እና በሳቸው ያመኑት ምእመናን በምን ሁኔታ ላይ ነበሩ?

መልስ- ሙሽሪኮች ምእመናንን ወደ አቢሲኒያ ነጉሥ እንዲሰደዱ እስኪፈቀድ ደረጃ ድረስ በእርሳቸውና በሙስሊሞች ላይ ግፋቸውን አጧጧፉት።

ሙሽሪኮች ነብዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለመጉዳት እና ለመግደል በአንድ ድምፅ ተስማምተውም ነበር። ይሁን እንጅ አላህ እሳቸውን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከሙሽሪኮቹ ለመታደግ አጎታቸው አቡጧሊብን ከለላ አደረገላቸው።

Open lesson
19ጥ 19፡- ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መልዕክተኛ ከሆኑ በአሥረኛው ዓመት የሞተው ማን ነበር?

መልስ- አጎታቸው አቡጣሊብ እና ባለቤታቸው ኸዲጃ ረዲየሏሁ ዓንሀ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

Open lesson
20ጥ20፡ ኢስራእ እና ሚዕራጅ ያደረጉት መቼ ነበር?

መልስ - እድሜያቸው ሃምሳ ሲሆን ነበር። ያኔም ነው አምስቱ ሶላቶች በግዴታነት የተደነገጉላቸው።

ኢስራእ ማለት ከመስጅደል ሐረም ወደ መስጅደል አቅሷ ያደረጉት ጉዞ ነው።

ሚዕራጅ ማለት ደግሞ ከአል'አቅሷ መስጅድ ወደ ሰማይ እስከ ሲድራቲል ሙንታህ ድረስ ያደረጉት ጉዞ ነው።

Open lesson
21ጥያቄ 21፡ ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከመካ ውጪ ያሉ ሰዎችን እንዴት ነበር ዳዕዋ ሲያደርጉላቸው የነበረው?

መልስ - ከመዲና የሆኑ አንሷሮች እሳቸው ዘንድ መጥተው በሳቸው አምነው በዳዕዋውም እንደሚተባበሯቸው ቃል እስኪገቡላቸው ድረስ ሰዎች የሚሰባሰቡባቸው በዓላትና አጋጣሚዎችን ጠብቀው ሰዎች ፊት እየቀረቡ ዳዕዋ ያደርጉ ነበር፤ የጧኢፍ ሰዎችንም ዳዕዋ ያደርጉላቸው ነበር።

Open lesson
22ጥ 22፡ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መካ ውስጥ ዳዕዋ እያደረጉ ለምን ያህል ጊዜ ቆዩ?

መልስ - አሥራ ሦስት ዓመታት ነው የቆዩት።

Open lesson
23ጥያቄ 23፡ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሂጅራ ያደረጉት ወዴት ነው?

መልስ - ከመካ ወደ መዲና ነው።

Open lesson
24ጥ 24፡ በመዲና ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ ቆዩ?

መልስ - ለአሥር ዓመታት ቆይተዋል።

Open lesson
25ጥ 25፡ ከእስልምና ህግጋት መካከል በመዲና ሳሉ የተደነገጉት ምን ምን ናቸው?

መልስ - ዘካ፣ ፆም፣ ሐጅ፣ ጂሃድ፣ አዛን እና ሌሎችም የእስልምና ህግጋቶች በመዲና ሳሉ የተደነገጉ ናቸው።

Open lesson
26ጥ 26፡ ዋና ዋና የሚባሉት ዘመቻዎቻቸውን ጥቀስ?

መልስ - የታላቁ በድር ዘመቻ፤

የኡሑድ ዘመቻ፤

የአሕዛብ ዘመቻ፤

(ፈትሑ መካ) መካ የተከፈተችበት ዘመቻ፤

Open lesson
27ጥ 27፡ ከቁርኣን መጨረሻ የወረደው ምን የሚለው ነው?

መልስ- ተከታዩ የላቀው አላህ ቃል ነው፦ {በእርሱም ውስጥ ወደ አላህ የምትመለሱበትንና ከዚያም እነርሱ የማይበደሉ ሲሆኑ ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ሥራ የምትሞላበትን ቀን ተጠንቀቁ። 281} [ሱረቱል በቀራህ፡ 281]

Open lesson
28ጥ 28፡ ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን መቼ ነው የሞቱት? ዕድሜያቸውስ ስንት ነበር?

መልስ - በአስራ አንደኛው አመተ ሂጅራ በወርሀ ረቢዑል አወል በስልሳ ሶስት አመታቸው አረፉ።

Open lesson
29ጥ 29፡ የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሚስቶች ስም ጥቀስ?

መልስ-1- ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

2- ሰውዳህ ቢንት ዘምዓህ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

3- ዓኢሻህ ቢንት አቢ በክር አስ'ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

4- ሐፍሷ ቢንት ዑመር ረዲየላሁ ዐንሃ፤

5- ዘይነብ ቢንት ኹዘይማህ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

6- ኡሙ ሰለማህ ሂንድ ቢንት አቢ ኡመያህ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

7- ኡሙ ሐቢባ ረምላህ ቢንት አቢ ሱፍያን ረዲየላሁ ዐንሃ፤

8- ጁወይሪያህ ቢንት አል'ሓሪሥ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

9- መይሙናህ ቢንት አል-ሓሪሥ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

10- ሶፊያ ቢንት ሑየይ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

11- ዘይነብ ቢንት ጀሕሽ ረዲየላሁ ዐንሃ፤

Open lesson
30ጥ 30፡ የነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ልጆች እነማን ናቸው?

መልስ - ሦስቱ ወንዶች ልጆቻቸው፦

አል-ቃሲም፤ የነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ቅጽል ስማቸውም በእርሱው ነበር የተሰየመው (አበል ቃሲም ይባሉ ነበር)።

ዐብደላህ፤

ኢብራሂም፤

ሴት ልጆቻቸው፦

ፋጢማህ፤

ሩቂያህ፤

ኡሙ ኩልሡም፤

ዘይነብ፤

ከኢብራሂም በቀር ሁሉም ልጆቻቸውን ከኸዲጃ (ረዲየላሁ ዐንሀ) የተወለዱ ናቸው። ከፋጢማህ በቀር ሁሉም እርሳቸው በህይወት እያሉ የሞቱ ሲሆን ፋጢማህ የሞተችው ግን እርሳቸው ከሞቱ ከስድስት ወር በኋላ ነበር።

Open lesson
31ጥ 31፡ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የተክለ ሰውነት መገለጫ ባህሪያት ጥቂቱን ጥቀስ?

መልስ - ረዥምም አጭርም ያልሆኑ በሰዎች መካከል መካከለኛ ቁመት፤ የአላህ ሶለዋትና ሰላም ይስፈንባቸውና ነጭ ሆኖ ቅላት የጠጣ ፊት ነበራቸው። ወፍራም ፂም፣ ሰፋፊ ዓይኖች፣ ተለቅ ያለ አፍ፣ ፀጉራቸው እጅግ የጠቆረ፣ ትከሻቸው የሰፋ እና ደስ የሚል መአዛ እንዲሁም ከዚህም ውጭ የመልካም ተክለ ሰውነት መገለጫ ባህርይ ነበራቸው።

Open lesson
32ጥ 31፡ ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኡመታቸውን (ህዝባቸውን) የተዉት በምን ሁኔታ ላይ ነው?

መልስ - ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኡመታቸውን ጥፋ ያለው ካልሆነ በቀር በማይሳሳትበት ነጭ ሆኖ ፍንትው ባለ ግልፅ ማስረጃ ላይ ነው የተውት። የትኛውንም ኸይር ነገር ኡመታቸውን ጠቁመዋል፤ ከየተኛውም ሸር ነገር ደግሞ ኡመታቸውን አስጠንቅቀዋል።

Open lesson